” ከቤተ ክርስቲያንና ከሀገር ተሰድዶ የነበረውን መጽሐፍ ከግእዝ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ በመሠራጨት ላይ ነው።

የመጽሐፉ ተርጓሚ

“#የትርጓሜን ጸጋ እንደ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የተላበሱ፥ የአንድምታ ትርጓሜን ሳይለቁ፥ የዘመኑን አንባቢ ሳይረሱ፥ ሁሉን ወደ ትርጓሜ የሚስቡ መጋቤ ምሥጢር ያሬድ ዘርእ ቡሩክ የድሪዳዋ ርእሰ አድባራት ወገዳማት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል የቅኔና የመጽሐፍ ትርጓሜ መምህር የዮሐንስ መደብር በትርጓሜ መርከባቸው አሳፍረው ንባቡን ከትርጓሜው፥ ትርጓሜውን ከምሥጢሩ አዋሕደው ጳውሎሳዊ ሃይማኖት፥ ዕውቀትና ሕይወትን እናገኝ ዘንድ ይኽን መጽሐፍ እንድንመገበው አቅርበዋል ።#ርዕስ_#ዮሐንስ መደብር

የህትመት ዘመን-ሚያዝያ ፳፻፲፮ ዓ.ም
#ተርጓሚና አሳታሚ ፦መጋቤ ምሥጢር ያሬድ ዘርእ ቡሩክ
_ የገጽ ብዛት 529

ዋጋው _700 ብር ($50)

ዮሐንስ መደብር ፦ 122 ምዕራፎች አሉት ።
_ከጀርባው የመጽሐፉን ረቂቅ በንስር ዐይናቸው የተመለከተለ ሊቃውንት አስተያየት አስቀምጠዋል ።
የቦሌ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል የመጻሕፍት መምህር መጋቤ ሐዲስ መልአከ አማረ ” ቤተ ክርስቲያን ምክነት የሌለባት ደም የማትቆርጥ ወላዲ ናት 2000 ዘመናትም አስቆጥራ ወላጆችን ትወልዳች፤ ..ከቤተ ክርስቲያንና ከሀገር ተሰድዶ የነበረውን ይህን ግሩም መጽሐፍ መልክዐ ፊደሉን ጠንቅቀው ፣ንባቡን አቅንተው ያልተመለሰውን መልሰው ከግእዝ ወደ አማርኛ ትርጓሜውን ተርጉመው ሐተታ የሚያስፈልጋቸውን በመምህራን ይትባሃል አትተው አቅርበውታል ደግመው ይውለዱልን ” ብለዋል።
#መታሰቢያነቱ፦መታሰቢያነቱ ለብፁዕ አቡነ ዶ/ር አረጋዊ ፣ለመጋቤ ምሥጢር ሄኖክ ተስፋኢየሱስ፣እና ለእመ ብዙሓን መምህርት መብራት ዘርይሁን በማለት ባለውለታዎቻችን አስበዋል

ስለ ጸሐፊው ፦ በድሪዳዋ ርእሰ አድባራት ወገዳማት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል የቅኔና የመጽሐፍ ትርጓሜ መምህር ናቸው ። ” የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው”(፪ቆሮ 11÷28)
የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ጉዳይ በመንፈሳዊ ቅናት ከሚያንገበግባቸው መምህራን መካከል መጋቤ ምሥጢር ያሬድ ዘርእ ቡሩክ አንዱ ናቸው ።
[ ] ብፁዕ አቡነ በርቶሎሜዎስ የድሪዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ “….ከ1300 ዓመታት በላይ ከአማርኛ ቋንቋ ጋር ሳይተዋወቅ የቆየው ይህ መንፈሳዊ መጽሐፍ በግእዝ በአማርኛ ጎን በጎን ምቹ ሁኖ በመታተሙ ገዝታችሁ ብታነቡት ብዙ ዕውቀት እንደምታገኙበት ሙሉ እምነት አለኝ”ብለዋል ።
[ ] ዮሐንስ መደብር መጽሐፍ ይዘት በአጭሩ ፦
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ታሪካቸው ያልተሟሉትን አሟልቶ ይዟል። ” ኢየሱስም ያደረገው ብዙ ሌላ ነገር ደግሞ አለ፤ ሁሉ በእያንዳንዱ ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት ዓለም ራሱ ባልበቃቸውም ይመስለኛል።”(ዮሐ.21፥25) በዓለም ላይ የነገሡትን የተለያዩ ሀገራት ኃያላን ነገሥታት ሙሉ ታሪካቸውን ይተርካል ። _ከ1_7ኛው ክ/ዘመን ድረስ የተነሡትን ቅዱሳን ሊቃውንት ያስቀምጣል ።መፍቀሬ መጻሕፍት ከቤታችን መኖር ያለበት ታሪካዊ ሥራ ነው። “#ዘቦ ዕዝን ሰሚዐ ለይስማዕ (ማር.፬፥፱፣ማቴ፲፩፥፲፭፣) ★ ★ ★ መ/ር ተመስገን ዘገዬ

ፈዋሴ ዱያን ጊዮርጊስ እምነ ከራድዮን ዖፍ ።ስምዐኒ ጸሎትየ ወስእለትየ ዘዘልፍ። #ኦ አምላከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዕቀበኒ ወአድኅነኒ እመከራ ሥጋ ወነፍስ ሊተ ለወልደ ሥላሴ !
ሚያዝያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም

━━━━━━━༺✞༻━━━━━

Leave a comment